Monday, September 12, 2016

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት

በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉት ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያ ውስጥ ከአመጋገብና ከኑሮ ዘይቤ መቀየር ጋር አብረው የመጡ ስኳር፣ ደም ግፊትና የተለያዩ አይነት የካንሰር በሽታዎች ተጠቂ ቢኖሩም ለነዚህ በሽታዎች በመጠኑም ቢሆን እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የኩላሊት ሕመም ምን ያህል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሌሎች የጤና ችግሮችን እንደሚያስከትል ማህበረሰቡ በቂ እውቀት የለውም።  የግንዛቤ እጥረት ችግር ከመኖሩም በላይ ከነጭራሹ ሁለቱም ኩላሊቶች ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ምክንያት የማሽን እጥበት የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መጥቷል እጥበቱም በወር በአማካኝ 15,000 እስከ 20,000 የኢትዮጵያ ብር የሚጠይቅ በመሆኑ መክፈል የማይችል ታማሚ እቤቱ ተኝቶ የሞቱን ጊዜ መጠባበቅ ምርጫው ሆኗል።

በአንድ ወቅት የተጠና ጥናት እንደሚያሳየው በአገራችን 2 ሚልዮን በላይ በኩላሊት ህመም ችግር እየተሰቃዩ የሚገኙ ሰዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ የኩላሊት እጥበት ዲያሊሲስ የሚያስፈልጋቸው 40ሺህ ይደርሳሉ። ከነዚህም ሰዎች አቅም 300 የሚበልጡ አይደሉም። ሕመሙ ኖሮበት ከላይ የተጠቀሱትን የሕይወት ፈተና ለመጋፈጥ የቻለ ሰው ቤት ንብረቱን እየሸጠ የሚችለውን እያደረገ ቢገኝም ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅሙ በመዳከሙ ተስፋው እየደበዘዘ የሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል እየሆነ መጥቷል።

የችግሩን አሳሳቢነት በመመልከት ችግሩን በተቻለ መጠን በዘላቂነት ለመፍታት በማስብ 43 በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ተሰባስበው የኩላሊት እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅቱን ለመመሥረት በቅተዋል። ይህንን ድረጅት በህመሙ እየተሰቃዬ ካሉት መሀከል 43 ሆነው ያቋቋሙት ሲሆን ከፌደራል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ምዝገባ ቢሮ ድርጅቶችን ማህበራት ኤጀንሲ ምዝገባ ቢሮ ሕጋዊ ዕውቅና የተሠጠው ይህ ድርጅት ይዞት በተነሳው ዓላማ በብቸኝነት የሚጠቀስ ሀገር በቀልና መንግስታዊ የልሆነ ድርጅት ነው።

የማኅበሩ አባላት 
የችግሩ ተቋዳሾች በሆኑ ሰዎች የተመሠረተው የኩላሊት አጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት በአሁኑ ወቅት መስራች ከነበሩት 43 ሰዎች መሃል አንድ ቢቀሩም በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ ከ500 በላይ የሚሆኑ በሽታው የተጠቁ የማህበር አባላት ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ከ16-30 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ቤተሰብ የመሠረቱ ናቸው።

 የማኅበሩ ዓላማ 
- የማኅበሩ ዋና ዓላማ በኩላሊት ህመም ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ሆነው የህክምና አገልግሎቱን በክፍያ ምክንያት ማግኘት ላልቻሉ ዜጎች ሁሉ አስፈላጊውን አገዛ በማድረግ ካሉበት የህምም ሰቃይ እፎይ ለማሰኘት ፣ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ 

ሰብእናቸው አድጎና ሰብአዊ ክብራዠው ተጠብቆ በዘላቂነት ምርታማ የሀገሪቷ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ እና ህብረተሰቡ በ ሰፊው   ስለ ኩላሊት ህመም እና ራሱን ከህመሙ እንዴት መጠበቅ እንደለበት በቂ መረጃ በመስጠት ራሳቸውን የሚከላከሉበትን የግንዛቤ ትምህርት ማስጨበጥ።
የዓላማው ማስፈፀሚያ ስልቶች 
· የግንዛቤ ማጎልበቻ መንገዶች ማመቻቸት።
· በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ውስጥ መሳተፍ።
· የማኅበረሰቡን አመለካከት በመለወጥ ዜጎች በበሸታው እንዳይጠቁ ማድረግ።
· የምክክር አገልግሎት በመስጠት የተሰበረ ሥነ-ልቦናቸውን መጠገን።
·  ከሚመለከታቸው መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ካልሆኑ መሰል ተቋማት ጋር ቅንጅት በመፍጠር በጋራ መንቀሳቀስ።

የማኅበሩ ተግባራዊ ዕቅዶች 
· ከተለያዩ አካላት ጋር በመስራት በአገር ውስጥና በውጪ በመንቀሳቀስ ማህበሩ የራሱን ወጪ የሚሸፍንበትን የገቢ  ምንጮች መፍጠርና ሁኔታዎችን በማመቻቸት ሙሉ በሙሉ የማሸን አጥበቱን /ዲያሊስስ/ ወጪያቸውን በመሸፈን።
· የአቻ ለአቻ ትምህርት ዘዴን በመጠቀም ለ1000,000 ለሚደርሱ ሰዎች ስለ ኩላሊት ህመም እና ራሱን ከህመሙ እንዴት መጠበቅ እንዳለበት በቂ መረጃ በመስጠት ራሳቸውን የሚከላከሉበትን የግንዜቤ ትምህርት ማስጨበጥ።
· የጤና አቅርቦቶችን በተሟላ ሁኔታ ማመቻቸት።
· የኩላሊት ዝውውር ወይም ንቅለ ተከላ የሚከናወንበትን የህክምና ተቋም በመገንባት ሥራውን በፍጥነት ማስጀመር
· በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች የኩላሊት ህመምተኞች የህክምና አገለግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት።

የማኅበሩ ውጤታማ ተግባራት 
· ማኅበሩ  በአሁኑ ጊዜ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፖታል ቅጥር ግቢ ውስጥ የተሰጠውን ቢሮ በማደሰና የራሱ ቢሮን በማስገንባት ስራውን ጀምሯል።
· እስከ ስድስት የዲያሊሲስ ማሽን ከጳውሎስ ሆስፒታል እንዲገኝ በማድረግ ከዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ጋር ለመስራት ዝግጅቱን ጨርሷል።
· ከደም ባንክ ጽ/ቤት አስፈላጊ  በሚሆንበት ጊዜ የደም ባንክ ዲያሊሲስ ለሚያደርጉ የማህበሩ አባላት ደም እንዲያገኙ ፈቃድ እግኝቷል።
·  ከግል የጤና ተቋማት በመወያየት በቅርቡ የዲያሊሲስ ሥራ አስከሚያስጀምር ድረስ የዋጋ ቅናሽ ለማህበሩ አባላቶች እንዲያደርጉ ስምምነት ላይ ደርሷል።
· ኤቪ ፊስቱላ እና ካቴተር ለማህበሩ አባላት በሚሰራላቸው ወቅት የህክምና ወጪውን ብቻ በማሽፈን እስከ 10000 ብር ድረስ ይከፍሉ የነበረውን ወጪ በ1/5 መቀነስ ችሏል። 
· ከጃፖን ኤምባሲ ከ10-20 የሚደርስ የዲያሊሲስ ማሽን ሊሰጠው ቃል ተገብቶለታል።


· 20  አልጋዎችን፤ 4 አስትሬቸር እና የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በእርዳታ ለማግኘት ችሏል።

· ማኅበሩ ባለው ሙሉ አቅም ለመንቀሳቀስ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ቢገኝም ከችግሩ ስፋትና ጥልቀት እንፃር ብዙ ተሠርቷል ማለት አይቻልም። የኩላሊት አጥበት የሚያስፈልጋቸው በርካታ የማህበሩ አባላት የድረጅቱን እና የሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ድጋፍና ዕርዳታ ይጠብቃሉ። ስለዚህም በቀጣይነት ውጤታማ ተግባራትን ለመፈፀም አቅዷል፡፡ ይህን ራዕዩን ለማሳካት ግን ያለበት የገንዘብ እጥረት ትልቅ ማነቆ ሆኖበታል። ችግሩ የሁሉም እንደመሆኑ አስፈላጊው ድጋፍና እገዛ ከተገኘ የማኅበሩ የነገ ህልም እውን መሆኑ እያጠራጥርም።   

No comments:

Post a Comment